የኮንሶ ደም ባንክ ማዕከል

ከጅምር ቅድመ-ዝግጅት ጥረቶች መካከል አንዱ የሆነው G+1 ዘመናዊ የኮንሶ ደም ባንክ ማዕከል!

የኮንሶ ልማት ማህበር ከካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የሆስፒታሉ የአገልግሎት ደረጃ ለማሳደግ የሚያግዙ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ዘመናዊ የደም ባንክ ማዕከል በቀጣዩ የሆስፒታሉ ደረጃ ለማሻሻል ከሚረዱ ማዕከላት መካከል አንዱ ከመሆኑ የተነሳ ልማት ማህበሩ ከሆስፒታሉ ጋር በከፍተኛ ትብብር ከወራት በፊት ዘመናዊ የደም ባንክ ማዕከል በስፒታሉ እንዲቋቋም ሊረዳ የሚችሉ ቅድሜ ዝግጅት ለማድረግ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙዎችን በማደራጀት፣ ልምድ ከሌላ ሆስፒታል እንዲወስዱ በማድረግ፣ የግንባታው ሥራ ዝርዝር ዕቅድና የዲዛይን ሥራ እንዲሠራ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፤ የጥሬቶችም በተግባር ታይቷልም፡፡ በዚህ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጋችሁ የሁለቱ ተቋማት ሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሁሉ ልማት ማህበሩ ልባዊ ምስጋና እያቀረበ ከዚህ በመቀጠል ሆስፒታሉ እንደተቋም ከመንግሥት ጋር በመተባበር በቀጣዩ ሊሠሩ የሚችሉ ሥራዎች ለማከናወን የተጀመሩ ሥራዎች ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል ብሎ ልማት ማህበሩ ያምናል፡፡

እንደሚታወቀው የኮንሶ ልማት ማህበር በአባላት መዋጮ ድጋፍ በሆስፒታሉ በ484 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ ባለ16 ክፍሎች ዘመናዊ የድንገተኛ ህክምና ማዕከል ህንፃ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ይህ አሻራ የአባላትና የልማት ደጋፊዎች ከፍተኛ የድጋፍ ውጤት ነውና አባል ያልሆኑ ሁሉ አባል በመሆን የቀጣዩ የግንባታ ሂደት ሥራዎች እንዲታጠናቅቁና የጀመራችሁት ታሪካዊ አሻራ ሙሉ በሙሉ እንዲታጠናቅቁ ልማት ማህበሩ ይጠይቃል፡፡

ከታች በተጠቀሱ የልማት ማህበር የአባልነት መዋጮ አካውንቶች መዋጮውን በማጠናከር የተጀመረውን ታርካዊ ታርክ ባጭር ጊዜ ውስጥ ከግብ እንዲታደርሱና ሪቫን እንዲትቆርጡ ልማት ማህበሩ የከበረ ጥሪውን ያቀርብላቸዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/Commercial Bank of Ethiopia፡ KDA MEMBERSHIP: 1000056457888

  • አብሲኒያ ባንክ/Abyssinia Bank: Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 83591536
  • ወጋገን ባንክ/Wogagen Bank፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 0914657910401
  • በዳሽን ባንክ/Dashen Bank፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 0354287288011
  • በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ/Lion International Bank፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 30711771653
  • በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ: Bunna International Bank፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 2459601000025
  • በአዋሽ ባንክ/Awash Bank፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 01308735205200
  • በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ/ Cooperative Bank of Oromia S.C፡ Konso Development Association–Membership & Funds: Account No: 1055300013678

የተከበራችሁ ውድ አባላትና የልማት ደጋፊዎች የአባልነት መዋጮ ወደ ኮንሶ ልማት ማህበር ዋናው ቢሮ በአካል ቀርበው አሊያም በባንኮች በአካውንቶች ማስገባትና መረጃውን በKonso Development Association/KDA FB page messenger or telegram(+251911269944፣ +251916698100) ላይ በቀላሉ መላክ ይቻላል።

ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው!

ኮንሶ ልማት ማህበር

ነሐሴ 19/ 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *